በ COVID-19 ጊዜ ጥንቃቄ በተሙላ መንገድ ለመሰብሰብ የሚጠቅሙ መመሪያዎች

Multilingual Resources

Image

ቢከተቡም ባይከተቡም ፣ በዚህ ብልግ ወራት ከጓደኛዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር  ለመሰብሰብ እያቀዱ ከሆነ ፣ እራስዎን እና የሚወዱትን ሰው ከ COVID-19 ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ያስቡ።

ክተባት መከተብ እራስዎን እና በአካባቢዎ ያሉትን በተለይም ለመከተብ ገና ብቁ ያልሆኑትን ሰዎች ለመጠበቅ በጣም አስተማማኝ የሆነ መንገድ ነው። ክትባቶቹ ከባድ ሕመምን እና ሞትን ለመከላከል በጣም ውጤታማ ናቸው፣ ነገር ግን ለመሰብሰብ ከወሰኑ ፣ ቢከተቡም ባይከተቡም ፣ COVID-19 ኢንፌክሽንን የመስፋፋት አደጋ ይኖረዋል። ክትባት መከተብ፣ የፊት ጭንብል መልበስ ፣ እጅን መታጠብ እና ከታመሙ እቤትዎ ውስጥ መቆየት ሌሎች ሰዎችን ከበሽታው ለመጠበቅ ሊወስዷቸው የሚችሏቸው እና ያሉ እርምጃዎች ናቸው።

የሕዝብ ስብሰባዎች

በአጠቃላይ ፣ በአሁኑ ጊዜ በህዝብ ውስጥ የሚሰበሰቡ ከሆነ፦

 • ክትባቱን መከተብ እራስዎን ከከፍተኛ ሕመም ፣ ሆስፒታል ውስጥ ከመተኛት ወይም በ COVID-19 ምክንያት ከመሞት ለመጠበቅ የተሻለው መንገድ ነው።
 • ማስክ ያድርጉ. ቢከተቡም ባይከተቡም እድሜያቸው አምስት አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በሁሉም የቤት ውስጥ የህዝብ ቦታዎች ላይ ፣ እንዲሁም ከቤት ውጭ በሚደረጉ ዝግጅቶች 500 እና ከዚያ በላይ ሰዎች በሚገኙበት ለምሳሌ ኮንሰርቶች ወይም ስፖርታዊ ዝግጅቶች ላይ የፊት መሸፈኛ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። እድሜያቸው ከ 2 እስከ 4 አመት የሆኑ ልጆች የፊት ጭምብል እንዲለብሱ አጥብቀን እንመክራለን።
 • በቤትዎ ይቆዩ ከታመሙ ወይም ምንም አይነት ምልክት ከታየብዎት።
 • አስቀድመው እቅድ ያውጡ. እራስዎን ደህንነቱ ባልተጠበቀ ወይም በማይመች ቦታ ውስጥ ለምሳሌ ጭንብል ያላደረጉ ሰዎች በተጨናነቀ ቡና ቤት ውስጥ ካገኙ ፣ ወደ ቤትዎ ይሂዱ ወይም ለመሄድ አማራጭ መንገዶችን ይፈልጉ።
 • WA Notify ን በስልክዎ ላይ ይጫኑ. ይህ COVID-19 ተጋልጠህ እንደሆነ ያስጠነቅቀሃል እና አዎንታዊ ምርመራ ካደረግክ ማንነታቸው ሳይታወቅ ሌሎችን ያስጠነቅቃል። WA Notify ሙሉ በሙሉ ግላዉ የሆነ ነገር ነው እና ማን እንደሆንክ አያውቅም ወይም የት እንደምትሄድ አይከታተልም።

የግል ሰብሰባዎች

የማህበረስብ ሰብሰባ ከመካሄድዎ በፊት

 • የእንግዶችዎን ዝርዝር ይገምገሙ. ማን ማንን እየጋበዙ እንደሆነ ያስቡ። ገና ለክትባት ብቁ ያልሆኑ ትናንሽ ልጆችን ጨምሮ ለCOVID-19 ከፍተኛ ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች የመጡ ይሆን? እንግዶችዎ መከተብ ወይም አለመከተባቸውን ያውቃሉ? የማታውቁ ከሆነ, በዚህ መሰረት እቅድ ማውጣት እንዲችሉ መጠየቅዎ አስፈላጊ ነው።
 • አስቀድመው ያቅዱ. ብዙ ያልተከተቡ ቤተሰቦች ካሉ ወይም ለከባድ COVID-19 ህመም ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ያልተከተቡ ሰዎች ያጋጠሟቸው ቤተሰቦች ካሉ፣ በጣም አስተማማኝ የሆነው አማራጭ በኦንላይን(ቨርቹዋል) መሰብሰብ ነው። በአካል ለመሰባሰብ ከወሰኑ፣ አብረዋቸው ጊዜ በምታሳልፉበት ወቅት ለደህንነት እንዴት ቅድሚያ እንደምትሰጡ ለጓደኞችዎ እና ለቤተሰብዎ ግልጽ ያድርጉ።
 • በሰላም ይጓዙ. ከቤተሰብዎ ወይም ከጓደኞችዎ ጋር ለመሰባሰብ ለመጓዝ እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን የCDC የጉዞ መመሪያን ይከተሉ። ከፍተኛ የ COVID-19 ስርጪት ወዳለበት አካባቢ እየተጓዙ ከሆነ፣ የፊት ማስክ በመልበስ እና ከሌሎች በህዝቦች 6 ጫማ (2 ሜትር) ያህል ርቀት ላይ በመቆየት የበለጠ ንቁ መሆን ያስፈልግዎታል።
 • ከቤት ዉጪ ያድርጉ. ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባዎች በቤት ውስጥ ከሚደረገው ይልቅ በጣም የተሻሉ ናቸው። የግድ ቤት ውስጥ መሆን ካለብዎት በደንብ አየር የሚነፍስበትን ቦታ ይምረጡ ለምሳሌ ክፍት መስኮቶች ያላቸው ክፍሎች።
 • በትንሹ ያድርጉ. ከቤተሰብ አባላትዎ ዉጪ ካሉ ሰዎች ጋር በሚሰበሰቡበት ግዜ አነስ ባለ ቁጥር መሰብሰብ የተሻለ ነው።
 • ያሳጥሩት.  አጠር ያለ ቆይታ COVID-19 ን የማስፋፋት እድሉ አነስተኛ ነው። አጭር ስብሰባዎች የእጅዎን እና የሰዉነትዎን ንጽህና በአግባቡ ለመጠበቅ ቀላል ያደርገዋል።
 • ልጅዎችን ከግምት ያስገቡ. ልጆች በስድስት ጫማ ርቀት የመቆየት ችግር ሊገጥማቸው ይችላል፣ ስለዚህ ጭምብል ማድረግ እና እጅን መታጠብ አስፈላጊ ነው። ያስታውሱ: ከ 2 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች በጭራሽ የፊት ጭምብል ማድረግ የለባቸውም! እድሜው ከ2 ዓመት በታች የሆነ የቤተሰብዎ አባል ከሆነ ወይም የፊት ጭምብል ማድረግ የማይችል ከሆነ ፣ ያልተከተቡ ወይም የክትባት ሁኔታቸው የማይታወቅ ሰዎችን የሚጎበኙበትን ብዛት ይቀንሱ።
 • የጤና ምርመራ ያድርጉ. ባለፉት 2 ሳምንታት ማንም ሰው እንደ ሳል፣ ትኩሳት ወይም የትንፋሽ ማጠር ያሉ ምልክቶች ካጋጠመው ይጠይቁ። ተጋባዥ እንግዶች ከመድረሳቸው በፊት የሙቀት መጠናቸውን እንዲታዩ ይጠይቋቸው። ማንኛውም ሰው ትኩሳት ያለው—ወይም ሌላ ምልክቶች ያጋጠመው ወይም COVID-19 ላለፉት ሁለት ሳምንታት መጋለጡን የሚያውቅ ሰው—ቤት መቆየት አለበት።
 • ይመርመሩ. ቢከተቡም ባይከተቡም ከስብሰባው 72 ሰዓታት በፊት በመመርመር የስርጪቱን አደጋ መቀነስ ይችላሉ። በቤት ውስጥ የሚደረጉ ምርመራዎችን በዝግጅቱ ቀን ሊጠናቀቁ ይችላሉ። ምርመራዎ ኒጌቲቭ ቢሆንም ፣ በዚህ ገጽ ላይ የተጋሩትን ሌሎች የደህንነት ጥንቃቄዎችን መከተል አሁንም ቢሆን አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው።
 • WA Notify ን በስልክዎ ላይ ይጫኑ. ይህ COVID-19 ተጋልጠህ እንደሆነ ያስጠነቅቀሃል እና አዎንታዊ ምርመራ ካደረግክ ማንነታቸው ሳይታወቅ ሌሎችን ያስጠነቅቃል። WA Notify ሙሉ በሙሉ ግላዉ የሆነ ነገር ነው እና ማን እንደሆንክ አያውቅም ወይም የት እንደምትሄድ አይከታተልም።

በግል ስብሰባው ወቅት

 • ማስክዎትን ያድርጉ.  ከቤተሰብዎ አባላት ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር በቤት ውስጥ የሚሰበሰቡ ከሆነ፣ አብዛኛዎቹ ተሰብሳቢዎች ሙሉ በሙሉ ካልተከተቡ በስተቀር ሁሉም ሰው የፊት መሸፈኛ እንዲያደርጉ ይመከራል። ምናልባት ሰዎች ረስተው ከመጡ እንኳን ተጨማሪ ጭምብሎች በእጃቸው ይያዙ።
 • እጅዎን ይታጠቡ. የመታጠብያ ሲንክ ለማግኘት ምንም እድል ከሌለ ፣ የእጅ ሳኒታይዘር ያዘጋጁ።
 • ርቀትን እና የቅርብ ንክኪን ይገድቡ. በተቻለበት ቦታ የ6 ጫማ ያህል ይራራቁ ፣ በተለይም ለ COVID-19 ከፍተኛ ተጋላጭነት ካላቸው ወይም እስካሁን ሙሉ በሙሉ ያልተከተቡ ሰዎች ጋር ሲሆኑ።
 • መስኮቶችን ይክፈቱ. ተገቢ የሆነ አየር እንዲኖር ለማድረግ ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው ክፍሎች ውስጥ መስኮቶችን ይክፈቱ።
 • ያጽዱ. ከመሰብሰብዎ በፊት እና በኋላ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቦታዎችን በተደጋጋሚ ያጽዱ።

በግል ከተሰበሰቡ በኋላ

 • እጅዎን ይታጠቡ(ደጋግመው). በሰሙና እና በዉሃ ለ 20 ሴከንዶች ይታጠቡ።
 • ሳኒታይዝ ያርጉ. በእንግዶች ሊነካኩ የሚችሉ እንደ ጠረጴዛዎች፣ የእርሳስ መቅረጫዎችን ፣ የበር እጀታዎች እና የመታጠቢያ ቤት እቃዎች ያሉ ሁሉንም ነገሮች በመጀመሪያ በሳሙና እና በውሃ እና ከዚያም በፀረ-ተባይ ማጽጃዎች ያፅዱ።
 • ምልክትዎችን ይከታተሉ. ማንኛውም አይነት ምልክቶች ከታየብዎት ምርመራ ያድርጉ።
  ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል ማንኛውም ሰው ተመርምሮ ፖዛቲቭ ከሆነ ለሌሎች ያሳውቁ። ለበሽታው ተጋልጠው ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ተጨማሪ ይማሩ።